Economy

ሱዳንና ኢትዮጵያ ታሪካዊ ቁርኝታቸውን ከፍ ወዳለ የኢኮኖሚ ትብብር ለማሸጋገር ተስማሙ

ሱዳንና ኢትዮጵያ ታሪካዊ ቁርኝታቸውን ከፍ ወዳለ የኢኮኖሚ ትብብር ለማሸጋገር ተስማሙ።

ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መገታት የሚገባው ችግር መሆኑ ላይም መግባባት ላይ ተደርሷል።

 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ዑመር ሃሰን አልበሽር ተወያይተዋል።

ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ካርቱም ላይ ከነበራቸው የ5ኛው የኢትዮ ሱዳን የጋራ ኢኮኖሚ ስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ ቆይታ ጎን ለጎን በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለቱ አገራት መካከል ለዘመናት የዘለቀውና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተው ታሪካዊና ቤተሰባዊ ግንኙነት በጽኑ መሰረት ላይ ወደተሸጋገረ የምጣኔ ሃብት ጥምረት እንዲሸጋገር ተስማምተዋል።

 

በዚህም የሃገራቱን ግንኙነት በንግድ፣ በመሰረተ ልማት ግንባታ በኢንቨስትመንት እና በሌሎች የኢኮኖሚ ማዕቀፎች ማስተሳሰር እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል።

ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን እና ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመግታት በጋራ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ይበልጥ ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑም ሁለቱ መሪዎች ከተስማሙባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው።

እንደውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ገለፃ በሁለቱ አገሮች መካከልም ሕጋዊ የሰራተኛ ስምሪት ማዕቀፍ ለመዘርጋት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የጋራ ጥናት ማድረግ ይገባል፡፡

ከሁለቱ አገሮች ተሰደው የሚኖሩ ዜጎቸ በፈቃዳቸው ወደየአገራቸው ለመመለስ ከፈለጉ በሁለቱም ወገን አስፈላጊው ድጋፍና ትብብር እንደሚደረግም ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ውይይት ስምምነት ላይ ደርሰዋል  ተብሏል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button