SportSports

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ ዛሬ ይጠበቃል

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ ዛሬ ይጠበቃል

 

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል፤ ዛሬ ደግሞ በርካታ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

 

የዕለቱ ተጠባቂ ግጥሚያ ቀን 9፡30 በሰሜን ለንደን ደርቢ ግጥሚያ ቶተንሃም ሆትስፐር ዊምብሌይ ላይ ከአርሰናል ጋር ይፋለማል፡፡ ይህ የደርቢ ጨዋታ በዛሬው ዕለት ለ198ኛ ጊዜ ይከናወናል፡፡ እስካሁን በተደረጉ ፍልሚያዎች መድፈኞቹ 82 ጊዜ ያህል በማሸነፍ የበላይነት አላቸው፡፡

 

ምሽት 12፡00 በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ ማንችስተር ሲቲ ወደ ዲን ኮርት አምርቶ ከቦርንመዝ፤ ብራይተን አሜክስ ላይ ከሀደርሰፊልድ፤ በርንሌ በቱርፍ ሞር ከክሪስታል ፓላስ፤ በኦልድ ትራፎርድ ማንችስተር ዩናይትድ ከሳውዛምፕተን ሲጫወቱ፤ ወልቭስ ሞሊኒክስ ስታዲዮም ላይ ከዌልሱ ካርዲፍ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

 

የዕለቱ የማሳረጊያ ግጥሚያ ዌስት ሃም ዩናይትድ በለንደን ኦለምፒክ ስታዲየም ከኒውካስትል ዩናይትድ ምሽት 2፡30 ይጫወታሉ፡፡

 

በፕሪምየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠራዥ ሊቨርፑል በ69 ነጥብ አናት ላይ ተቀምጧል፤ ማንችስተር ሲቲ በ68 ነጥቦች ይከተላል፤ ቶተንሃም በ60 ነጥብ 3ኛ፤ አርሰናል በ56 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፤ ማንችስተር ዩናይትድ በ55 5ኛ እንዲሁም ቼልሲ በ53 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button