EthiopiaHealth

በ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጭ የተገነባው ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች ማስወገጃ ማዕከል ስራ ሊጀምር ነው

በ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጭ የተገነባው ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች ማስወገጃ ማዕከል ስራ ሊጀምር ነው

አርትስ 25/03/2011

በ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጭ የተገነባው የአዳማ ከተማ ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች ማቃጠያ ዘመናዊ ማዕከል ከ 2 ሳምንት በኋላ ስራ አንደሚጀምር የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ማዕከሉን ጎብኝተዋል፡፡

ማዕከሉ ጊዜያቸው ካለፈባቸው መድሀኒቶች አወጋገድ ጋር ተያይዞ ከህብረተሰቡ የሚነሳውን ቅሬታ እንደሚፈታ ተነግሯል፡፡

ጊዜያቸው ያለፋባቸው መድሃኒቶችን በማስወገድ አቅም  በአፍሪካ የመጀመሪያው  እንደሆነ የተነገረለት ማዕከሉ  በሰዓት 1 ሺ ኪሎ ግራም ጊዜ ያለፈባቸውን መድሀኒቶች ማቃጠል የሚችል ነው ተብሏል።

በሌሎች 7 ቦታዎች ተመሳሳይ ማዕከላት እየተገነቡ ሲሆን፥ ከ 3 ወር በኋላ ወደ ስራ እንደሚገቡም ታውቋል።

እንደ ጤናጥበቃ ሚኒስቴር  መረጃ ይህን ማዕከል ጨምሮ በግንባታ ላይ ለሚገኙት ማዕከላት ከ 13 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጭ ተደርጓል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button