Uncategorized

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከበርካታ ሹማምንቶቻቸው ጋር ግላዊ ሚስጥራቸው ለሳይበር ምዝበራ መጋለጡ ተገለጸ

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከበርካታ ሹማምንቶቻቸው ጋር ግላዊ ሚስጥራቸው ለሳይበር ምዝበራ መጋለጡ ተገለጸ፡፡

 

የመራሂተ መንግስቷ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ  ባለስልጣናት የስልክ ግንኙነት ፣ የግል የስልክ ምልልሶችን  ጨምሮ የገንዘብ ዝውውር መረጃዎች ባልታወቁ ጠላፊዎች ተመንትፎ በድረ ገፅ መለለቁ እየተነገረ ነው፡፡

 

እንደ ቢቢሲ ዘገባ እስካሁን ከድርጊቱ ጀርባ የነማን እጅ እንዳለበት የታወቀ ነገር የለም ተብሏል፡፡

የመረጃው ይፋ መሆን የሚያስከትለው የጉዳት መጠን እስከአሁን በውል አልታወቀም ያሉት የፍትህ ሚኒስትሯ ካትሪና ባርሌይ ጥቃቱ ግን እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

ሚኒስትሯ ከጥቃቱ ጀርባ ያሉ ሰዎች ዓላማ የሀገሪቱን ዴሞክራሲ እና ተቋማዊ ተዓማኒነት ማሳጣት ነው ብለዋል ፡፡

 

የሀገሪቱ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ቢሮ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ የማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግሮ እሰካሁን ባለው መረጃ መንግስታዊ መረጃዎች አለመነካታቸውንም አረጋግጧል፡፡

 

በተደረገው የማጣራት ስራ ከባለስልጣናቱ በተጨማሪ ታዋቂ ግለሰቦች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን  ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

የጀርመን ባለስልጣናት ተመሳሳይ የሳይበር ምዝበራ  ሲደርስባቸው የመጀመሪያ አለመሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ እ.አ.አ በ2015 ሩሲያ በዴስታግ በሚገኘው  የጀርመን ፓርላማ  ላይ  የሳይበር ጥቃት ማድረሷ ይታወቃል፡፡

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button