SportSports

የቻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ተፋላሚ ቀሪ ቡድኖች ዛሬ እና ነገ ይለያሉ

የቻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ተፋላሚ ቀሪ ቡድኖች ዛሬ እና ነገ ይለያሉ

የ2018/19 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 16ቱ ቡድኖች የማጣሪያ የመልስ ቀሪ ግጥሚያዎች ዛሬ እና ነገ ምሽት ይከናወናሉ፡፡

በዛሬው ዕለት ሁለት ጨዋታዎች ሲከናወኑ፤ የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ በኢቲሃድ ሻልከን ምሽት 5፡00 ላይ የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ግጥሚያ ቬልቲንስ አሬና ላይ ሲቲ ራሂም ስተርሊንግ ባለቀ ሰዓት ባስቆጠራት ግብ ታግዞ 3 ለ 2 ድል ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በምሽቱ የመልስ ጨዋታ በውሃ ሰማያዊዎቹ በኩል አይምሪክ ላፖርቴ ከጉዳቱ ያገገመ ቢሆንም የጆን ስቶንስ ጤንነት ግን እየታየ ነው ተብሏል፤ ኒኮላስ ኦታሜንዲ እና ፈርናንዲንሆ በቅጣት ከጨዋታው ውጭ የሆኑ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ጓርዲዮላ በምሽቱ ለወጣት ተጫዋቾች የመሰለፍ ዕድል እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

ሌላኛው ፍልሚያ በተመሳሳይ ሰዓት ጣሊያን ምድር ላይ በዩቬንቱስ እና በስፔኑ አትሌቲኮ ዴ ማድሪድ መካከል ይካሄዳል፡፡

ጨዋታው በአሊያንዝ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን በመጀመሪያው የዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ግጥሚያ አትሌቲ 2 ለ 0 ድል በማድረግ ሰፊ የማለፍ ዕድልን ይዟል፡፡

አሮጊቷ ሩብ ፍፃሜውን ለመዋሃድ በአሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኔ የሚሰለጥኑትን ቀይ እና ነጭ ለባሾቹን ጥላ ለማለፍ፤ ግብ ሳታስተናግድ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጎሎችን ማስቆጠር ይጠበቅባታል፡፡ ሮናልዶ፣ ዲባላ እና ማንዙኪች የዩቬ ውጤት ቀልባሽ መመኪያ ቁልፍ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ነገ ደግሞ ባየርን ሙኒክ ከ ሊቨርፑል  እንዲሁም ባርሴሎና ከ ሊዮን የሚያደርጉት ይጠበቃል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button