Regions

በጌዲዮ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ለተፈናቃዮች ከሚደረገው ድጋፍ ጋር አለመመጣጠኑ ለተፈናቃዮቹ የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑን የሚያመላክት መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

በጌዲዮ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ለተፈናቃዮች ከሚደረገው ድጋፍ ጋር አለመመጣጠኑ ለተፈናቃዮቹ የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑን የሚያመላክት መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

በሌላ በኩል መንግስት በጌዲኦ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ጥረት እያደረግኩ ነው ይላል፡፡

መጋቢት 23 ቀን 2010 አ.ም ጀምሮ ነው  ከጌድዮ ዞን የገደብ ወረዳ ጎቲቲ ቀበሌ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀል የጀመሩት፡፡

በዚህም ግጭቱ ተነሳ በተባለበት ጊዜ ወደ መቶ 45 ሺህ የሚደርሱ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበረ ሲሆን ቆይቶም የተፈናቃዮች ቁጥር ወደ 7 መቶ ሃምሳ  ሺህ መጨመሩን ከብሄራዊ አደጋ እና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአሁኑ ሰአት ከጌዲዮ ዞን ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ እና በ6 የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጎች ቁጥር 2 መቶ 8 ሺህ 2 መቶ 75 መድረሱን በብሄራዊ አደጋ እና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአቅርቦት እና ሎጂስቲክስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አይድሩስ ሁሴን ለአርትስ ቲቪ ገልፀዋል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ገዙ አሰፋ ከዚህ ቀደም በሰጡት መግለጫ ከእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመሆን ችግሩን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ ተከናውኗል ብለው ነበር፡፡

በ6 መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው  የሚገኙት ተፈናቃዮች ቁጥርም አሁንም አልቀነሰም፡፡

እንደውም መፈናቀሉ  ቆይቶ  በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙትን ጨምሮ ባለፈው አመት በተነሳው ግጭት ተፈናቅለው ያልተመለሱና በተለያዩ ጊዜያት ከመሮሪያቸው ወጥተው በዘመዶቻቸው ቤትና በተለያየ ሁኔታ የተጠለሉዜጎች ቁጥር አጠቃላይ 2 መቶ 8 ሺህ 2 መቶ 75 መድረሱን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

በምዕራብ ጉጅ ዞን መንግስት በአካባቢው ታጣቂዎች ላይ በወሰደው እርምጃ ስጋት ነው ነዋሪዎቹ ከገደብ ወረዳ ጎቲቲ ቀበሌ የተፈናቀሉት ቢልም በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ  ተፈናቃዮች  ግን ጥቃት እንደደረሰባቸው ይናገራሉ፡፡

በብሄራዊ አደጋ እና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአቅርቦት እና ሎጂስቲክስ ዳይሬክተር አቶ አይድሩስ እንደነገሩን የክልሉ መንግስት ለኮሚሽኑ የድጋፍ ጥያቄ ባለማቅረብ ነው ኮሚሽን መስሪያቤቱ እስከአሁን ለተፈናቃዮች ድጋፍ ያላደረገው፡፡

በመሆኑም  ኮሚሽኑ በማህበራዊ ድረገፆች የተሰራጩትን መረጃዎች የሚያጣራ ቡድን በቦታው መላኩን ሰምተናል፡፡

ለጊዜው ግን ምስሎቹ ተፈናቃዮች ሃይል ሰጪ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው የሚያሳዩ በመሆናቸው  በትላንትናው እለት ሁለት መቶ ኩንታል ሃይል ሰጪ ብስኩቶች፣ አልሚ ወይም ሲ ኤስ ቢ ፕላስ የሚባሉ የምግብ አይነቶችን፣ አተር ክክ እና ዘይት ወደ ቦታው መላኩን ዳይሬክተሩ ነግረውናል፡፡

ኮሚሽን መስሪያቤቱ ይህን ይበል እንጂ የጌዲዮ ተፈናቃዮች በዋናነት ድጋፍ እየተደረገላቸው ያሉት መንግስታዊ ባልሆኑ ኤን ጂኦዎች ጥምረት መሆኑን የተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የተቋማቱን ተወካዮች ጠቅሰው ዘግበዋል፡፡

በከጌዲዮ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር እና እየተደረገ ያለው ድጋፍ የሚመጣጠን ባለመሆኑ ለዜጎች ዘላቂ የሆነ መፍትሄ የሚያመጡ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው ፣ጉዳዩም ትኩረት የሚያሻው ነው፡፡

በበርካታ የአገሪቱ ክፍል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በየአካባቢው በተቀሰቀሱ ግጭቶች ሳቢያ እየተፈናቀሉ መሆኑም ይታወቃል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button