Breaking News

ዛሬ ምሽት በዩሮፓ ሊግ አርሰናል ተጠባቂ ጨዋታውን ያደርጋል  

ቼልሲ ወደ ዩክሬን አምርቶ ከዳይናሞ ኬቭ ጋር ይፋለማል፡፡

የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ግጥሚያዎች በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ዛሬ ምሽት የሚካሄዱ ይሆናል፡፡

ምሽት 2፡55 ላይ የማውሪዚዮ ሳሪው ቼልሲ ወደ ዩክሬን አምርቶ ከዋና ከተማው ቡድን ዳይናሞ ኬቭ ጋር ይፋለማል፡፡ ባለፈው ሳምንት ሁለቱ ቡድኖች ባደረጉት ግጥሚያ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ሰማያዊዎቹ 3 ለ 0 በማሸነፋቸው፤ ወደ ሩብ ፍፃሜው የማለፍ ተስፋቸው ከፍ ያለ ነው፡፡

ጎንዛሎ ሂግዌን ከቡድኑ ጋር ወደ ኬቭ ያልተጓዘ ተጫዋች ነው፡፡

የእንግሊዙ አርሰናል በመጀመሪያው ዙር ያስተናገደውን የ3 ለ 1 ሽንፈት ለመቀልበስ ኤመሬትስ ላይ ከፈረንሳዩ ሬን ጋር ምሽት 5፡00 ሲል ይፋለማል፡፡

መድፈኞቹ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ግብ ሳያስተናግዱ ከ2 ለ 0 በሚነሳ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ፈረንሳያዊው አሌክሳንደር ላካዜት ከቅጣት መልስ ለጨዋታው ዝግጁ መሆኑ ሲነገር፤ አርሜኒያዊው አማካይ ሄንሪክ ምኪታሪያን ለጨዋታው ያለው ዝግጁነት እስካሁን አልታወቀም፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች አር. ቢ ሳልዝበርግ ከ ናፖሊ፣ ክራስኖዳር ከ ቫሌንሲያ፣ ቤንፊካ ከ ዲናሞ ዛግሬብ፣ ኢንተር ሚላን ከ አይንትራክት ፍራንክፉርት፣ ስላቪያ ፕራሃ ከ ሲቪያ እና ቪያሪያል ከ ዜኒት ፒተርስበርግ ይጫወታሉ፡፡

leave a reply