Sports

የአውሮፓ የኮከብ ተጫዋቾች ምርጫ ዛሬ ምሽት ይፋ ይደረጋል፡፡

በ2018/19 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የምድብ ድልድል ምሽት 12፡00 ሰዓት ላይ ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርአት ሲካሄድ የአውሮፓ የአመቱ የወንድና ሴት ኮከብ ተጫዋች፤ የ2017/18 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂ፣ የተከላካይ፣ አማካይ እና አጥቂ ተጫዋቾች ምርጫ ይፋ ይደረጋል፡፡
በዚህም ለወንድ ኮከብ ተጫዋችነት በእጩነት ሉካ ሞድሪች (ሪያል ማድሪድ)፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ (ዩቬንቱስ) እና ሞሀመድ ሳላህ (ሊቨርፑል) ቀርበዋል፡፡
በሴቶች፡ ፔርኒል ሀርደር (ወልፍስበር)፣ አዳ ሀገርበርግ (ሊዮን)፣ አማንዲን ሄነሪ (ፖርትላንድ ትሮንስ/ሊዮን) 
በግብ ጠባቂነት አሊሰን ቤከር (ሊቨርፑል)፣ ጃንጂ ቡፎን (ፒ.ኤስ.ጂ)፣ ኬይለር ናቫስ (ሪያል ማድሪድ)
በተከላካይ መስመር ማርሴሎ፣ ሰርጂዮ ራሞስና ራፋኤል ቫራን ሁሉም ከሪያል ማድሪድ
በአማካይ ስፍራ ኬቨን ዴ ብሩይኔ (ማንችስተር ሲቲ)፣ ሉካ ሞድሪች (ሪያል ማድሪድ)፣ ቶኒ ክሮስ (ሪያል ማድሪድ)
በአጥቂ መስመር ሊዮኔል ሜሲ (ባርሴሎና)፣ ክርስትያኖ ሮናልዶ (ሪያል ማድሪድ)፣ ሞሀመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)
በተጨማሪም በዩሮፓ ሊግ የ2017/18 ውድድር ኮከብ ተጫዋች ለመሆን በእጩነት ዲያጎ ጎዲን እና አንቶን ግሪዝማን ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ዲሚትሪ ፓየት (ማረሴ) ቀርበዋል፡፡
የእርስዎን የምድብ ድልድል እና የኮከብ ተጫዋች ግምት ይንገሩን፡፡

አርትስ ስፖርት 24/12/2010

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button