Uncategorized

በኮንጎ በደረሰ የባቡር አደጋ 32 ሰዎች ህይዎታቸው አለፈ፡፡

በኮንጎ በደረሰ የባቡር አደጋ 32 ሰዎች ህይዎታቸው አለፈ፡፡

በዲሞክራክ ንጎ ካሳይ በተባለች ግዛት በጭነት ባቡር ይጓዙ በነበሩ መንገደኞች ላይ ነው አደጋው የደረሰው ተብሏል፡፡

በአደጋው ሳቢያ ከሞቱት 32 ሰዎች በተጨማሪ ከ17 በላይ ተጓዦች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ከአደጋው ተጎጅዎች መካከል አብዛኞቹ ህፃናት መሆናቸው ታውቋል፡፡

የሀገሪቱ ፖሊስ  የባቡሩ ሰረገላዎች ሀዲዱን ስተው ወንዝ ውስጥ በመግባታቸው  ለአደጋው የተጋለጡ ሰዎችን ፈልጎ ማግኘት አስቸጋሪ አድርጎታል ብሏል፡፡

አሁንም ፍለጋው ስላልተጠናቀቀ የሟቾችም ሆነ የቁስለኞች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ነው ፖሊስ እና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተናገሩት፡፡

የአደጋው መንስኤ ገና ያልታወቀ ቢሆንም በኮንጎ በስራ ላይ ያሉት ባቡሮች አብዛኞቹ ከ 1960ዎቹ ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጡ እና በቂ ጥገና የማይደረግላቸው መሆኑ አደጋውን ሳያስከትል እንዳልቀረ ብዙዎቹ ይገምታሉ፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button