EthiopiaNews

በደቡብ ክልል የአስፈጻሚ ተቋማት የ2012 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የስራ ክንውን ግምገማ ተጀመረ ።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012  በደቡብ ክልል የአስፈጻሚ ተቋማት የ2012 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የስራ ክንውን ግምገማ ተጀመረ ።የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ ተቋማት በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት እንደሚገመገሙ ተመልክቷል።የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በግምገማው መድረክ እንደገለጹት በክልሉ ለውጡን ተከትሎ የተፈጠሩ ችግሮችን በመፍታት የህዝብን ደህንነትና ሠላም ለማረጋገጥ መንግሥት የወሰዳቸው እርምጃዎች ውጤታማ ናቸው።ከአደረጃጀት፣ መልካም አተዳደርና ልማት ጥያቄዎች ጋር ተያይዞ ተፈጥሮ የነበረው የተዛባ አመለካከትና አለመተማመን ህዝብን በማዳመጥ ለመመለስ ጥረት ሲደረግ መቆየቱንም አውስተዋል።ከፌዴራል መንግስት ጋር በመቀናጀት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉንና የጸጥታ ችግር ከምንጩ ለማድረቅ የተከናወኑ ስራዎች መልካም እንደነበሩ አስረድተዋል።በተለይ የህዝብ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በተደረገው ጥረት የዘገዩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እንዲበቁ መመቻቸታቸውንም አስታውቀዋለ።መንግሥት የህዝብን እርካታ ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የፈጠረው ችግር ፈታኝ እንደነበር ጠቅሰው “ስርጭቱን ለመቆጣጠር ህዝብና መንግሥት ርብርብ እያደረጉ ነው ” ብለዋል።የክልሉ መንግስት አስፈጻሚ ተቋማትየበጀት ዓመቱ የስራ ክንውን ግምገማ ዓላማ የነበሩ መልካም ተሞክሮዎችን ለማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም በቀጣዩ ዘመኑ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲመቻቹ ለማስቻል ነው።አሁን ላይ የተቋማቱ የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ሪፖርት በክልሉ ፕላን ኮሚሽን በኩል እየቀረበ መሆኑንና በዚህ ላይ ግምገማው እንደሚቀጥል ሪፖርተራችን ከስፍራው ዘግቧል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button