EthiopiaSocial

ሐምሌ 28 በሚሌኒየም አዳራሽ የቤተክርስትያን አንድ መሆንን አስመልክቶ ልዩ ጉባዔ ይካሄዳል፡፡

ጉባዔዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አራተኛ ፓትሪያሪክ የሆኑት የብፁዕ አቡነ መርቆሪዎስ አቀባበል አንዱ አካል ነዉ ተብሏል፡፡
የጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሚሊኒየም አዳራሽ ሀምሌ 28 ቀን 2010ዓ.ም የሚደረገዉ ጉባዔ የቤተክርስቲያን ልደት በመሆኑ ታላላቅ የሀይማኖት አባቶች፤ ህዝበ ክርስትያኑ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ አምባሳደሮችና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በጉባኤዉ የቤተክርስትያን አንድነትና ለሀገር ቀጣይነት ያለዉ ሰላም ማምጣት ላይ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button