AccidentAfrica

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኒው ዮርክ ታይምስን ዘገባ አጣጥሎታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኒው ዮርክ ታይምስን ዘገባ መሰረተ ቢስ ሲል አጣጥሎታል፡፡

ኒው ዮርክ ታይምስ አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪ ተገቢውን የምስለ በረራ ስልጠና አልወሰደም የሚል አንድምታ ያለው ዘገባ አሰራጭቷል፡፡

አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ በተለይ የአደጋው መንስኤ ገና እየተጣራ ባለበት ወቅት ይህን መሰል ሚዛናዊነት የጎደለው ዘገባ ማራጨት ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ማሳሳት ነው ብሏል፡፡

ፓይለቶቻችን አዳዲስ አውሮፕላኖች ባስመጣን ቁጥር ማብረር ከመጀመራቸው አስቀድሞ አስፈላጊውን ስልጠና ከአምራች ኩባንያው በሚሰጠው ማሳሰቢያ እና ኤፍ ኤኤ ባፀደቀው መሰረት ስልጠናዎችን ወስደዋል ብሏል ተቋሙ፡፡

ኒው ዮርክ ታይምስ ለአየር መንገዱ ቅርብ የሆኑ ሰዎችን አናገርኩ ብሎ ያሰራጨው ዘገባ የተዛባ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኢትየጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ህጉ በሚያዘው መሰረት የመረጃ ትንተናውን ውጤት በትግእስት እየተጠባበቀ መሆኑን ተናግሯል፡፡

በተለይ በኢንዶኔዥያ አደጋ ከደረሰ በኋላ የአሜሪካው ኤፍ ኤኤ ያወጣውን መመሪያ ሁሉም አብራሪዎች እንዲያውቁት አስፈላጊው ገለፃ ከመደረጉም ባሻገር የመመሪያው ሙሉ ይዘት በስልጠና ማንዋል ተካቷልም ብሏል አየር መንገዱ፡፡

ከዚህ በኋላም ቢሆን ሁሉም የመገናኛ ብዙሀን የምርመራ ውጤቱ ተጠናቅቆ ለህዝብ ይፋ እስከሚሆን ድረስ ከመሰል አሳሳች ዘገባዎች መቆጠብ እንዳለባቸው ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button