Breaking News

ከ121 በላይ የጤና ባለሙያዎች ለጌዲዮ ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረግ ተልከዋል ተባለ፡፡

የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ቅኝቶችና የገንዘብ ድጋፍም ተደርጓል፡፡

ከ121 በላይ የጤና ባለሙያዎች ለጌዲዮ ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረግ ተልከዋል ተባለ፡፡

የጤና ሚኒስቴር ለጌዲዮ ዞን ተፈናቃዮች ድጋፍ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎችና የተለያዩ መድሃኒቶች እንዲሁም ሌሎች ግብአቶችን ወደ ስፍራው ልኳል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዋ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለፁት ካሁን በፊት ከክልል 10 ሐኪሞች ፣ 10 ነርሶች፣ 5 የአካባቢ ጤና ባለሙያዎች እና 5 የኢፒዲሞሎጂ ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ተልከዋል፡፡

የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ቅኝቶችና ዳሰሳዎች እንዲሁም  የገንዘብ ድጋፍም ተደርጓል፡፡

በዚህኛው ፕግራም ከአዲስ አበባ የተውጣጡ አምስት ሐኪሞች እና 26 ነርሶች እንዲሁም መድኃኒቶችና ሌሎች ግብዓቶች ከኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ወጪ ሆነው ወደ ስፍራው ተልከዋል ብሏ ሚኒስቴሩ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ ወደ ስፍራው ካቀኑት ከ121 በላይ የጤና ባለሙያዎች በተጨማሪ የተለያዩ መጠን እና አይነት ያላቸው መድሃኒቶች መላካቸውንና ይህ መሰሉ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

leave a reply