EthiopiaSocial

የደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ቢሰማሩ እንደሚያዋጣቸዉ አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ተናገሩ ።

የደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ቢሰማሩ እንደሚያዋጣቸዉ አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ተናገሩ ።

በደቡብ ኮሪያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ሽፈራው ኮሪያን ሄራልድ ከተባለ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የሁለቱን አገራት ህዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሰፊ የንግድና ኢንቨስትመንት አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለኮሪያ ባለሃብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን ጠቅሰው ለአብነትም ያላትን ሰፊ የሰው ሃይልና ተመራጭ የጂኦግራፊ አቀማመጥ አንስተዋል።
በኮሪያ ቆይታቸው የአገሪቱ ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መዋለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጠንክረዉ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት እንዳገኘነዉ መረጃ ኢትዮጵያውያን በኮሪያ የትምህርትና ስልጠና እድል እያገኙ ሲሆን  እስካሁን 400  ኢትዮጵያዊያን በትምህርትና ስልጠና እድሉ ተጠቃሚ ሆነዋል

 

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button