EthiopiaPolitics

የሀገሪቱን ወቅታዊ ጉዳይና  የለዉጡን አንድ ዓመት በተመለከተ  ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ማብራሪያ ተሰጠ

የሀገሪቱን ወቅታዊ ጉዳይና  የለዉጡን አንድ ዓመት በተመለከተ  ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ማብራሪያ ተሰጠ
ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታና ባለፈው አንድ ዓመት የተገኙ ድሎችን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ማብራሪያውን የሰጡት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የፕሬስ ጉዳዮች ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም ናቸው።

በኢትዮጵያ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በኢኮኖሚ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ወ/ሮ ሂሩት በገለጻቸው ዳሰዋል።

በዚህም በርካታ እስርኞች መፈታታቸው፣ በውጭ አገራት የሚኖሩ ፖለቲከኞችና ነፍጥ አንግበው ከመንግስት ጋር ሲዋጉ የነበሩ ሃይሎች ወደ አገር ቤት መምጣታቸው፣ በሰብዓዊ መብት አያያዝና የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች የፖለቲካ ዘረፍ ስኬቶች ናቸው ብለዋል።

በኢኮኖሚ ዘርፍም የአጠቃላይ የአገሪቱን የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚጠቁም ጥናት በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጸው ሲጠናቀቅም ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ከዚህም ባሻገር መንግስት ያለበትን የእዳ ጫና በማቃለል እና የበጀት ቋትን በማጠናከር ረገድ ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኑን ተናግረዋል።

“እስካሁን ከመጣንበት የኢኮኖሚ አካሄድ ተሞክሮዎችን በመውሰድና ከተለመደው አሰራር በመውጣት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ እምርታ የሚያሸጋግር አጠቃለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ክለሳ ሂደት ውስጥ ነን” ሲሉም ነው ወ/ሮ ሂሩት የገለጹት።

ኢትዮጵያ በቅርቡ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ማጽደቋን ጠቅሰው ይህም መንግስት ኢኮኖሚውን ክፍት ለማድርግ ላላው ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለዋል።

መንግስት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ ከምንጊዜውም በላቀ ቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም እስካሁን ያሳየውን አጋርነት እንዲገፋበት እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ በኢጋድ ማዕቀፍ ጨምሮ በቀጣናው ያላትን ገንቢ ሚናም አጠናክራ እንደምትቀጥል ወ/ሮ ሂሩት ገልጸዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የፕሬስ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም በበኩላቸው መንግስት አየተካሄደ ያለውን ለውጥ ዘላቂ ለማድረግ ለተቋማት ግንባታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።

ለውጡም በህዝቡ ዘንድ በባለቤትነት እንዲያዝ በቅርቡ ምሁራንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፈሎችን ያካካተ “አዲስ ወግ” የተሰኘ የውይይት መድረክ በማዘጋጀት እስካሁን የተገኙ ድሎችን ገምግሟል ብለዋል። ይህም እንደሚቀጥል በመጠቆም።

በመጨረሻም ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

 

 

 

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button