EthiopiaSportSports

በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በኢትዮጵያውያን የተመዘገቡ የሩጫ ውጤቶች

በኔዘርላንድስ ሮተርዳም ማራቶን በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አሼቴ በከሬ በ2፡22፡55 ስታሸንፍ፤ ኬንያዊቷ ስቴላ ባሮሲዮ 2፡23፡36 ሁለተኛ እንዲሁም ሌላኛዋ ኬንያዊ አትሌት አሊፍን ቱሊያሙክ በ2፡26፡50 ሶስተኛ አትሌት ቤተልሔም ሞገስ አራተኛ ደረጃ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡

በወንዶች ኬንየዊው ማሪዩስ ኪፕሴሬም ፤ ቱርካዊው ካን ኦዝቢሌን እና ኢማኑኤል ሳይና ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ኬንያዊያን የበላይነት በነራቸው የሚላን ማራቶን በሴቶች ቪቪያን ኪፕላጋት ጄሮኖ በ2፡22፡25 ቀዳሚ ስትሆን ሌላኛዋ ኬንያዊት ጆአን ኪገን ጄፕቺርቺር በ2፡32፡32 ሁለተኛ እና ኢትዮጵያዊቷ አየሉ አበበ ሆርዶፋ በ2፡ 37፡ 50 ሶስተኛ ደረጃን ስትይዝ ብዙወርቅ ካሳዬ ጌታሁን አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን ፈፅመዋል፡፡

በወንዶች ደግሞ ኬንያውያኑ ቲቱስ ኢኪሩ ፤ ኢቫንስ ቺቤት ኪፕላጋት እና ኢድዊን ኮኢች ኪፕንጌቲች ተከታትለው በመግባት አሸናፊ ሁነዋል፡፡  

በሮም ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ሲቀናቸው፤ በወንዶች ተባሉ ዛዉዴ ሄይ በ2፡ 08፡ 37 ፤ተስፋ ጥሩነህ ወርቅነህ በ2፡ 09፡ 17 እና ይሁንልኝ አዳሜ አምሳሉ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ፤ ሙሳ ባዶ ኢዶ እና ብርሃኑ ተሾመ ደምሴ አራተኛና አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን ፈፅመዋል፡፡

በሴቶች የተካሄደውን ውድድር አትሌት መገርቱ አለሙ በ2፡ 2፡22፡ 52 አንደኛ ፤ ሙሉሃብት ፀጋ በ2፡26፡ 41 ሁለተኛ እና ጫልቱ ነገሰ በ2፡30፡ 45 ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

በብራዚል ሳው ፖሎ ማራቶን በሴቶች ሲፋን መላኩ ደምሴ በ2፡ 35፡ 03 አሸናፊ ሁናለች፡፡

በኦስትሪያ ቬና ማራቶን በወንዶች ታደሰ አብርሃም ሁለተኛ ደረጃ ይዟል፡፡

በፖላንድ ዴድኖ ማራቶን በወንዶች ኬንያዊው ቦኒፌስ ዋምቡ በ2፡ 16፡ 47 አሸናፊ ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ ታረቀኝ ዘውዱ፣ ፍቅሩ ዳዲ እና ሙሉ ቱሉ ከሁለት እስከ አራተኛ ደረጃ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡

በፖላንድ ሎድዝ ማራቶን በወንዶች ጌታዬ ገላው 2፡ 14፡ 39 አሸናፊ ሁኗል፡፡

በጀርመን ሀኖቨር ማራቶን በወንዶች አለባቸው ደባስ ዋለ ሶስተኛ፤ አብደላ ጎዳና ገመዳ አንዲሁም በሴቶች ትግስት ማሙዬ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል፡፡

በማድሪድ ግማሽ ማራቶን ትግስት ተሾመ፣ ሃዊ መገርሳ እና አበበች ሙሉጌታ፣ ኦብሴ አብዴታ እና አበሩ አያና ከ 1 – 5ኛ ደረጃ ተከታትለው በመግባት አሸናፊ መሆን ችለዋል፡፡

በወንዶች ተስፋዬ አበራ ሁለተኛ ሲወጣ ፤ ገብሬ እርቂሁን አራተኛ ደረጃ ላይ ጨርሰዋል፡፡

ኢስታንቡል ግማሽ ማራቶን አባይነህ ደጉ በወንዶች ሁለተኛ እንዲሁም ሔለን ቶላ እና ነፃነት ጉደታ ሶስተኛና አራተኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡

በዋሽንግተን ቼሪ ብሎሶም 10 ማይል ርቀት ጀማል ይመራ በ45፡ 36 ሰከንድ ቀዳሚ በመሆን አሸናፊ ሁኗል፡፡

 

የመረጃው ምንጭ አፍሪካን አትሌቲክስ ዩናይትድ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button