Middle EastPolitics

ኔታኒያሁ በፓርላማ ምርጫ አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ኔታኒያሁ በፓርላማ ምርጫ አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታናያሁ ከ120 የምክር ቤት መቀመጫዎች መካከል 65 ወንበሮችን በማግኘት ወደፊት የሚመሰረተውን የጥምር መንግስት ለመምራት የሚያስችላቸውን ድል አስመዝግበዋል ነው የተባለው፡፡

ሮይተርስ በዘገባው ለእስራኤላዊያን በሙስና መንጀል ተጠርጥረው ክስ የሚጠብቃቸውን ኔታኒያሁን መምረጥ ከሪፈረንደም አይለይም የሚል ፅሁፍ አስነንብቧል፡፡

እስካሁን የመራጮች ድምፅ 97 በመቶ ተቆጥሮ ያለቀ ሲሆን ውጤቱ የሚያሳየው ኔታኒያሁ አሸናፊ መሆናቸውን ነው፡፡

የኔታያሁ ደጋፊዎች ውጤቱን እንደሰሙ ተሰባስበው አርሱ ተዓምረኛ መሪያችን ነው በማለት ከፍ ባለ ድምፅ ድጋፋቸውን አሰምተዋል፡፡

የኔታናያሁ ቀንደኛ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት የቀድሞው የእስራኤል የጦር አዛዥ ቤኒ ጋንትስ በበኩላቸው በምርጫ አሸናፊዎች ነን  እርግጡን ለማወቅ ግን የምርጫውን ጠቅላላ ውጤት መጠበቅ ግድ ይለናል ብለዋል፡፡

የጥምር መንግስት በመመስረቱ ሂደት ኔታኒያሁን ከሰልጣን የማባረር እድል እንዳለ እና እሱን ለማድረግ የቀናት እድል እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል ጋንትስ፡፡

ኔታኒያሁ ዳግም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እስራኤልን ከመሩ በሀገሪቱ ታሪክ ብዙ ዓመታትን በመምራት አዲስ ታሪክ ያስመዘግባሉ፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button