EthiopiaRegionsSocial

የላሊበላ ዉቅር አብያተክርስትያናት መጠለያ እንዲነሳ ገንዘብ እያሰባሰበ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

አርትስ 29/01/2011

ሚኒስቴሩ መጠለያዉን በሰሩት ባለሞያዎች ለማስነሳት 300 ሚሊየን ብር ያስፈልገኛል ብሏል፡፡

የሚኒስቴሩ የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ፋንታ በየነ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጥናት ተካሄዶ መጠለያዎቹ እንዲነሱ ቀድሞ የተወሰነ ቢሆንም በጀት ባለመኖሩ ሊፈጸም አልቻለም ብለዋል፡፡

ጉዳዩን ግን አስከ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ድረስ አድርሰናል ያሉት አቶ ፋንታ፤በተለየ በጀት እንዲመደብም ጠይቀን ነበር ብለዋል፡፡

አሁን ለመጠለያዉ ማንሻ ገንዘብ እያሰባሰብን ነዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ  ቤተክርስትያንም በገንዘብ በኩል ድጋፍ ማድረግ አለባት ብለዋል፡፡

ገንዘቡ ከተገኘ መጠለያዉ በሚነሳበት ሁኔታ ላይ መጠለያዉን ከሰራዉ ድርጅት ጋር ተወያይተናል፡፡አቤያተክርስትያናቱ ከታደሱ በኋላ መጠለያዉ ተነስቶ በሌላ ቀላል መተጠለያም እንደሚተካ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዉ ነግረዉናል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button