loading
1 ሺህ 77 የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወሰነ። 

1 ሺህ 77 የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወሰነ።

የአዲስ አበባ ግብር ከፋይ የሆኑ እና ጉዳያቸው በፖሊስ እና በአቃቤ ህግ ተይዞ የነበሩ 1 ሺህ 77 ነጋዴዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወሰነ።

የከተማ አስተዳደሩ የአዲስ አበባ ግብር ከፋይ የሆኑ ክሳቸው እንዲቋረጥና ፍርድ የተሰጠባቸው በምህረት እንዲለቀቁ ለፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ነዉ ክሳቸዉ የተቋረጠዉ

መዝገቦች እጅግ አነስተኛ የገንዘብ መጠን የያዙ ሆነው ያለ ደረሰኝ እና ከዋጋ በታች ግብይት የተከናወነባቸው፣ ደረሰኝ ሳይዙ ዲኪላራይሶን ሳይኖራቸው የተለያዩ ዕቃዎች በንግድ ሱቃቸው የተገኘባቸው፣ የባለስልጣኑን ስራ በማሰናከል እና ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳርያ አድራሻ ጋር የተፈፀሙ ጥፋቶች በመሆናቸው እነዚህ ወንጀሎች ከአፈፃፀማቸው ፣ ከያዙት የገንዘብ መጠን አነስተኛ መሆን እንዲሁም ከተያዘው የታክስ ሪፎርም እና ከግለሰቦቹ የኢኮኖሚ አቅም አንፃር በምርመራ እና በፍ/ቤት ደረጃ ያሉ በሙሉ እንዲቋረጡ ቢደረጉ በመንግስት እና በህዝብ ጥቅም ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ዝቅተኛ በመሆኑ ክሳቸው ተቋርጦ ወደ ስራ ቢገቡ የሚያበረክቱትን አስተዋፅዖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወስኗል፡፡

ከመርካቶ የታክስ ሪፎርም አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ያደረጉት ኢ/ር ታከለ ኡማ መንግስት የንግዱን ማህበረሰብ ችግር ለመፍታት የሚሄደውን ርቀት ያህል ግብር ከፋይ ነጋዴውም የሚገባውን ግብር በወቅቱ በመክፈል ኃላፊነቱ እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *