Breaking News

ኢትዮጵያ ቡና ለምርጡ ደጋፊው ክብር ሰጥቷል

ይህ ሰው ከ22 ዓመታት በላይ በእግር ኳሱ የድጋፍ አበርክቶ ቆይታ እንደነበረው ይነገራል፡፡

በትላንትናው ምሽት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ቤተሰብ አንድ ወዳጃቸውን ግን እንደ ብዙ የሚመለከቱትን የልብ የሆነ ሰዋቸውን እና ባለውለታ እስከመባል የደረሰውን የደጋፊዎች ፊትአውራሪ አዳነ ሽጉጤ ምስጋና ሰጥተዋል!!!

የኢትዮጵያ ቡና ምልክት የሚል ቦታ የተሰጠው፤ ለረጅም ዓመት በአዲስ አበባ ስታዲየም ሚስማር ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በማስጨፈር ክለቡን ሲደግፍ የነበረው አዳነ ሽጉጤን በምሽቱ በርካታ ተጋባዥ እንግዶች ፣ የክለቡ አመራሮች እና ቡናማ ደጋፊዎች ፤ አርቲስቶች እና የእግር ኳስ ቤተሰቦች በተገኙበት ለኢትዮጵያ ቡና ስላበረከተው ነገር ሁሉ ክብር እና ውዳሴ ይገባሃል በማለት በወዳጆቹ ታጅቦ ተመስግኗል፡፡

አዳነ ሽጉጤ ከተወዳጅ የክለብ ድጋፉ በተጨማሪ የብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታዎች ላይ ከሌሎች ክለቦች ደጋፊዎች ጋር በመተባበር ደመቅ ያለ ድጋፉን ሲሰጥ ነበረ፡፡

አዳነ የሚስማር ገዥነቱን ለማመልከት ቡናማ ወንድሞቹ ፡

‹‹የተቆላ ቡና እሚመስለው ፊቱ

አደነ ሽጉጤ ሚስማር ላይ ነው ቤቱ›› እያሉ አዚመውለታል፡፡

ይህ ሰው ከ22 ዓመታት በላይ በእግር ኳሱ የድጋፍ አበርክቶ ቆይታ እንደነበረው ይነገራል፡፡

leave a reply