AfricaSportSports

የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ዛሬ ምሽት ይፋ ይሆናል

በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ግብፅ አስተናጋጅነት የሚሰናዳው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የምድብ ድልድል ዛሬ ምሽት 2፡00 ላይ ካይሮ ውስጥ ይፋ ይደረጋል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ከጥር ወር ወደ ሰኔ ወር ተሸጋግሮ በ24 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የሚከናወነው ይህ ውድድር በጉጉት ይጠበቃል፡፡

ከፕሪምየር ሊጉ ኮከቦች መካከል የሊቨርፑል ተጫዋቾች መሀመድ ሳላህ (ግብፅ) እና ሳዲዮ ማኔ (ሴኔጋል) ፤ የማንችስተር ሲቲው ሪያድ ማህሬዝ (አልጀሪያ) ፤ እንዲሁም የክሪስታል ፓላሱ ዊልፍሬድ ዛሃ (አይቮሪ ኮስት) የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱን ይጠብቁታል፡፡

ብሔራዊ ቡድኖቹ በመጋቢት ወር የፊፋ የሀገራት ደረጃ መሰረት በአራት ቋት የተደለደሉ ሲሆን በእያንዳንዱ ቋት ስድስት ቡድኖች ይኖራሉ፡፡

ቋት 1፡ ግብፅ ፣ ካሜሮን፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ናይጀሪያ እና ሞሮኮ

ቋት 2፡ ዲ.ሪ ኮንጎ፣ ጋና፣ ማሊ፣ አይቮሮ ኮስት፣ ጊኒ እና አልጄሪያ

ቋት 2፡ ደቡብ አፍሪካ፣ ዩጋንዳ፣ ቤኒን፣ ሞሪታኒያ፣ ማዳጋስካር እና ኬንያ

ቋጽ 4፡ ዚምባብዌ፣ ናሚቢያ፣ ጊኒ ቢሳው፣ አንጎላ፣ ታንዛኒያ እና ቡሩንዲ ተካትተዋል፡፡ በአጠቃላይ በውድደሩ ስድስት ምድቦች ይኖራሉ፡፡  

ካፍ ውድድሩን እንድታሰናዳ ቅድሚያ ዕድል ሰጥቷት ከነበረችው ካሜሮን፤ ነጥቆ ከወራት በፊት ለግብፅ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከሰኔ 12እስከ ሐምሌ 12/2011 ዓ/ም ይከናወናል፡፡  

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button