EthiopiaSportSports

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ ይከናወናሉ

የሊጉ የ20ኛ ሳምንት መርሀግብር ጨዋታዎች በነገው ዕለት ሲጀመሩ ፤ በዕለቱ በብቸኝነት የሚከናወነው ጨዋታ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ሲል መቐለ ላይ በአሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌ የሚመራው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በትግራይ ስታዲየም በስዩም ከበደ ከሚመራው መከላከያ ይጫወታል፡፡

የሳምንቱ ቀሪ ጨዋታዎች በበነጋታው ዕሁድ የሚከናወኑ ሲሆን ስድስቱ ጨዋታዎች በክልል ስታዲየሞች እንዲሁም አንዱ አዲስ አበባ ላይ ይደረጋል፡፡

ክልል ላይ የሚደረጉት ግጥሚያዎች በተመሳሳይ 9፡00 ላይ ይደረጋሉ፡፡

በሳምንቱ መርሃግብር ተጠባቂ ከሆኑት ጨዋታዎች መካከል አንዱ የሆነው የባህር ዳር ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ በግዙፉ የባህር ዳር ስታዲየም ይደረጋል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ካላቸው ወቅታዊ አቋም አንፃር የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል፡፡ ጨዋታውን አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ የምትመራው ይሆናል፡፡

የጎንደሩ ፋሲል ከነማ በፋሲለደስ ስታዲየም ወደ ወራጅ ቀጠናው የተመለሰውን ደቡብ ፖሊስ ያስተናዳል፡፡ አፄዎቹ በሜዳቸው በሚያደርጉት ግጥሚያ ደረጃቸውን ለማሻሻል ይጠቀሙበታል ቢባልም የደቡቡ ቡድን በቀላሉ አጅ አይሰጥም፡፡

እዛው ሰሜን ኢትዮጵያ ላይ ቆይታ ስናደርግ ከሁለተኛው ዙር በኋላ መነቃቃት እያሳየ የሚመስለው ደደቢት በትግራይ ስታዲየም ላይ የምስራቁን ድሬዳዋ ከነማ ጋር ይፋለማል፡፡

በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አዳማ ከተማ የደቡቡን ሀዋሳ ከተማ ይገጥማል፡፡

ወደ ድል ጎዳና የተመለሰው ኢትዮጵያ ቡና ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ተጉዞ ሶዶ ላይ ወላይታ ድቻን ይጎበኛል፡፡ ጅማ አባ ጅፋር ደግሞ ሜዳው ላይ የትግራዩን ስሑል ስሁል ሽረ የሚገጥም ይሆናል፡፡

የሳምንቱ ሌላኛው ተጠባቂ ጨዋታ እና ማሳረጊያ ፍልሚያ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ሲደረግ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ የደረጃ ሰንጠራዥ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ሲዳማ ቡና ጋር ይፋለማል፡፡

መቐለ 70 እንደርታ የሊጉ የደረጃ ሰንጠራዥ አናት ላይ በ42 ነጥቦች እና 16 ንፁህ ግቦች ታጅቦ አሁንም ቀዳሚ ነው፤ ሲዳማ ቡና በ34 ነጥብ ይከተላል፡፡ ፋሲል ከነማ በ33 ነጥቦች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ጥሩ የውድድር ዓመት እያሳለፈ የማይገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ30 ነጥብ አራተኛ ነው፡፡

ባህር ዳር እና ቡና በዕኩል 29 ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው አምስተኛ እና ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት በሊጉ የደረጃ ሰንጠራዥ የመጨረሻዎቹ ቀዳሚ ክለቦች ናቸው፡፡

የመቐለው አጥቂ አማኑኤል ገብረሚካኤል በ12 ጎሎች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ይመራል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button