EconomyWorld News

ጃፓን እና ቻይና ጉርብትናችንን ማጠናከሩ ይበጀናል እያሉ ነው፡፡

ጃፓን እና ቻይና ጉርብትናችንን ማጠናከሩ ይበጀናል እያሉ ነው፡፡

ዲያዎዩ በተባለችው በሁለቱ ሀገራ ድንበር በምትገኘው ደሴት ለዓመታት ሲወዛገቡ የኖሩት ጃፓን እና ቻይና ጉርብትናቸውን ለመልካም ነገር በማዋል የኢኮኖሚ ትስስራቸውን ለማጠናከር  ቃል ገብተዋል፡፡

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የሁለቱ ሀገራት መልካም ግንኙነት አሁን   ወደቀደመው በታ ተመልሷል ብለዋል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ቶኪዮእና ቤጂንግ ስድስት ወሳኝ በሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎች በጋራ ለመስራ ተስማምተዋል፡፡

በቴክኖሎጂ በሀይል ቁጠባ እና አጠቃቀም፣ አንዲሁም በአካባቢ ጥበቃ እና በሌሎችም መስኮች አብረው ለመስራት ነው የተስማሙት፡፡

የጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታሮ ኮኖ በበኩላቸው ሁለቱ የዓለማችን የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶች ይህን መሰል ስምምነት ማድረጋቸው ለዓለም ኢኮኖሚ የሚተርፍ ስራ ይሰራሉ ብለዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቤጂንግ ባዘጋጀችው የጃፓንና የቻይና የወጣቶች ዓመታዊ የወዳጂነት ስነ ስርዓት ላይ ተገናኝተው ነው ስምምነቶቹን ያደረጉት፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button