EthiopiaSportSports

ኢትዮጵያዊያን ወጣት አትሌቶች አቢጃን ላይ ድል አስመዝግበዋል፡፡

ዛሬ አራተኛ ቀኑን ባስቆጠረውና 32 የአፍሪካ ሀገራት እየተሳተፉ ባሉበት ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ውጤታማ ባልነበረችባቸው የሜዳ ላይ ተግባራት ትናንት በአቢጃን ደምቃበት ውላለች።

ከ20 ዓመት በታች አዲር ጉር በስሉስ ዝላይ 15: 77 በመዝለል በዘርፉ ኢትዮጵያ በአህጉራዊ ውድድር የመጀመሪያውን ወርቅ አግኝታለች። በዛው ምድብ በከፍታ ዝላይ ዶፕ ሊም ከደቡብ አፍሪካዊ ተቀናቃኙ ጋር ከፍተኛ ፉክክር ካደረጉ በኋላ ለሀገሩ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡

በሌላኛው የሜዳ ተግባራት መርሀዊት ፀሀዬ ከ20 ዓመት በታች ምድብ የዲስከስ ውርወራ 45:97 በመወርወር የነሐስ ሜዳሊያ ስታገኝ፤ በዚህም የግሏ የነበረውን የኢትዮጵያን ክብረ-ወሰን አሻሽላለች ።

ከ18 ዓመት በታች በተደረው የ3000 ሜትር ውድድር ከሁለት ኬንያውያን ጋር ብርቱ ትንቅንቅ አድርጎ የሁለተኝነት ደረጃን በመያዝ ለሀገሩ ሌላኛውን የብር ሜዳሊያ ያስገኘው ይሁን ፋንታሁን ነው።

ከ18 ዓመት በታች ምንተስኖት አበበ በተሳተፈበት የመዶሻ ውርወራ ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝቷል።

መስከረም አበራ በ100 ሜ መሠናክል ማጣሪያ ሁለተኛ በመሆን ለፍፃሜ አልፋለች።

ከትናንት በስቲያ ከ20 ዓመት በታች በ3000 ሜትር መሰናክል ሎሚ ሙለታ የነሐስ ተሸላሚ ሁናለች።

ከ18 ዓመት በታች የ2000 ሜትር መሰናክል ታደሰ ታከለ ወርቅ አስመዝግቧል።

ተክኤን አማረ በ3000 ሜትር ከ18 ዓመት በታች የሴቶች የፍፃሜ ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።

የሴቶች ከ 18 ዓመት በታች የ1500 ሜትር ውድድር ድርቤ ወልተጂ ወርቅ ለሀገሯ አስገኝታለች። በወንዶች 1500ሜ ፍፃሜ መለሰ ንብረት ደግሞ ነሐስ ለሀገሩ አስገኝቷል።

በውድድሩ ኢትዮጵያ 4 ወርቅ ፣ 4 ብርና 8 ነሐስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

መረጃው፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button