AccidentAfrica

ሶማሊያ ውስጥ በቦንብ አደጋ የሞት እና የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡

ሶማሊያ ውስጥ በቦንብ አደጋ የሞት እና የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡

የሀገሪቱ ፖሊስ በሰጠው ማረጋገጫ ሞቃዲሾ ውስጥ በተሸከርካሪ ላይ በተጠመደ ፈንጂ  አራት ሰዎች ህይዎታቸው ሲያልፍ አምስቱ ደግሞ ቆስለዋል፡፡

ሲ ጂ ቲ ኤን የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው መካ አል ሙከረማ በተባለው የከተማዋ ክፍል ከባድ  የፍንዳታ ድምፅ የሰሙ ነዋሪዎች በእጂጉ ተደናግጠው ነበር፡፡

አንድ የግል የአምቡላንስ ድርጂት ዳይሬክተር የሆኑት ሞሀመድ አብዲከሪም ደግሞ አንድ አስከሬን እና 13 ቁስለኞችን ወደ ሆስፒታል ማጓጓዛቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለፈው መጋቢት ወር ላይ ሞቃዲሾ ውስጥ በአንድ ምግብ ቤት እና መንግስት ባለ ስልጣናት መኖሪያ ህንፃ ላይ በደረሱ የቦንብ አደጋዎች 30 ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button