SportSports

ላትሲዮ ለኮፓ ኢታሊያ ፍፃሜ አልፏል፤ ዛሬ ተጋጣሚው ይለያል

የ2018/19 የጣሊያን ኮፓ ኢታሊያ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ትናንት ምሽት ሲደረግ፤ ዛሬ ሌላኛው ግጥሚያ የሚከናወን ይሆናል፡፡

በአሰልጣኝ ጅናሮ ጋቱሶ የሚመራው ኤስ ሚላን ጁሴፔ ሚያዛ ላይ የሮማውን ቡድን ላትሲዮ አስተናዶ የ1 ለ 0 ሽንፈት ገጥሞት ለፍፃሜ ዋንጫው ሳይበቃ ቀርቷል፡፡

ላትሲዮም በደርሶ መልስ ጨዋታ የ1 ለ 0   ውጤት በማስመዝገብ የኮፓ ኢታሊያ ፍፃሜ ተፋላሚነቱን አረጋግጧል፡፡

የሮማውን ቡድን ወደ ፍፃሜው ያሻገረች ብቸኛ ግብ ከመረብ ያገናኘው ጁአኪን ኮሪያ ሲሆን ዛሬ ምሽት ተጋጣሚውን የሚያውቅ ይሆናል፡፡

ምሽት 3፡45 ላይ አታላንታ ቤርጋሞ ላይ ፊዮረንቲናን አትሌቲ አዙሪ ደ ኢታሊያ ላይ ያስተናግዳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ተጫውተው 3 ለ 3 አቻ መለያየታቸው ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button