Uncategorized

ከሰባት ሚሊዮን በላይ የየመን ህጻናት ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ

ከሰባት ሚሊዮን በላይ የየመን ህጻናት ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ

አርትስ 22/02/2011

 የተባበሩት መንግስታት የህጻናት ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በየመን ያለው ጦርነት ማብቃቱ  ብቻውን የህጻናቱን ህይወት ማዳን አይችልም።

በአሁኑ ወቅት ከአምስት አመት በታች ያሉ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን የየመን ህጻናት ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተጋለጡ ሲሆን 4 መቶ ሺህ የሚሆኑት ደግሞ  ለከባድ የመቀንጨር በሽታ ተጠቂ ሆነዋል ብሏል የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት  ዩኒሴፍ።

“ጦርነትን ማቆም በቂ አይደለም። የምንፈልገው ጦርነቱን አቁሞ ህዝብንና ህጻናትን ማዕከል ያደረገ የመንግስት ተግባር ሲከናወን ማየት ነው” ብሏል ዩኒሴፍ። ዘገባው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ነው።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button