Ethiopia

የኢሕአፓ ኢትየዮጵያን የአረብሊግና የኔቶ አባል የማድረግ ፍላጎት::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2013  አርትስ ቲቪ ያዘጋጀው የመጀመሪያ ዙር የፓለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ተካሂዷል፡፡ በክርክሩ ላይም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ፣ ህብር ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ኢህአፓ ተሳትፈዋል፡፡ ሶስቱ ፓሪቲዎች በስድሰተኛው ሀገራዊ ምርጫ አሸንፈው ስልጣን ቢይዙ ሊተገብሩ ባዘጋጁት የውጭ ጉዳይ እና የደህንነት ፖሊሲ ላይ ክርክር አድርገዋል፡፡

ኢዜማን ወክለው በክርክሩ የቀረቡት አቶ ግርማ ሰይፉ ፓርቲያቸው የሀያላን ሀገራትን ፍላጎትና የጥቅም ግጭቶችን ለመመከት የሚያስችል አማራጭ ፖሊሲ ማዘጋጀቱን ገልፀዋል፡ በደህንነት ጉዳይም ገዢው ፓርቲ እየተከተለ ያለውን ፖሊሲ በመቀየር የደህንነት መስሪያ ቤቶች በሙሉ በባለሙያ እንዲመራ ያደርጋል በተጨማሪም በብቃትና በትምህርት ዝግጅትም የላቁ ሰዎች እዲሰሩበት ይደረጋል ብለዋል፡፡

የህብር ኢትዮጵያ ተወካይ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በበኩለቸው የሳቸው ፓርቲ ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ የተቀዳ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በመፍጠር በእኩልነት ላይ ያተኮረ የውጭ ፖሊሲ ማዘጋጀቱን ገልፅዋል፡፡ ይህም ህብር ኢትዮጵያ ከብሔራዊ ጥቅም የመነጩ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ለመቅረፅ እንደሚታገል
ያሳያል ነው ያሉት፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ በመወከል በክርክር ምረኩ ላያ የታደሙት መጋቢ ብሉይ አብርሀም ሃይማኖት ኢ.ህ.አ.ፓ ለኢትዮጵያ የሚመጥናትን የውጭ እና ደህንነት ጉዳይ ፖሊሲ አዘጋጅቷል ብለዋል፡፡

ፓርቲያችን በምርጫው ቢያሸንፍ ኢትዮጵያ የኔቶና የአረብ ሊግ አባል እንድትሆን ይሰራል ሲሉም አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም በደህንነት ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያ የኢጋድ ሊቀ መንበርነት መልቀቅዋን እንደማይቀበልና ቦታዋን ደግማ እንድትይዝ የተቻለውን እንደሚያደርግ በክርክሩ ወቅት ገልፅዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button