Breaking News

አቶ ደመቀ መኮንን ከፕሬዝዳንት ሙሰቬኒ ጋር ተወያዩ 

አቶ ደመቀ መኮንን ከፕሬዝዳንት ሙሰቬኒ ጋር ተወያዩ 

አቶ ደመቀ መኮንን ከፕሬዝዳንት ሙሰቬኒ ጋር ተወያዩ

የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ በዩጋንዳ ኢንቴቤ ከተማ ከዩጋንዳ ፕሬዝዳንት  ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ጋር ተዋያይተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ኢንቴቤ ከተማ በሚገኘው ፅህፈት ቤታቸው አቶ ደመቀን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ከፍተኛ ባለሰልጣናት በቀጠናዊ ትብብር እና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።

በተለያዩ መስኮች ለረጅም ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ እና የዩጋንዳ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መግባባት ላይ ደርሰዋል።

ሁለቱ አገሮች በቀጠናው ዙሪያ በሚስተዋሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይም የተወያዩ ሲሆን በቀጣይ በቀጠናው ትብብራቸውን ለማጥጠቅ በሚችሉበት አግባብ ዙሪያ ተስማምተዋል።

አቶ ደመቀ በጉብኝታቸው ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶ/ር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ማድረሳቸዉን ከዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል

leave a reply