EthiopiaSocial

ንብረትነቷ የአቢሲኒያ ፍላይት የሆነች ሲስና 172 የመማሪያ አነስተኛ አውሮፕላን በጅማ አቅራቢያ ተከስክሳ በአብራሪው ላይ ጉዳት ደረሰ

ንብረትነቷ የአቢሲኒያ ፍላይት የሆነች ሲስና 172 የመማሪያ አነስተኛ አውሮፕላን በጅማ አቅራቢያ ተከስክሳ በአብራሪው ላይ ጉዳት ደረሰ
አውሮፕላኗ ዛሬ ጧት 4 ሰዓት ገደማ ላይ ጅማ ዞን አሰንዳቦ በተባለ አካባቢ ልምምድ ላይ እያለች የመከስከስ አደጋ ገጥሟታል፡፡

በአደጋው በአብራሪው ላይ ጉዳት እንደደረሰበት የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንሙት ለማ ለኢቲቪ ገልፀዋል፡፡

የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ተጨማሪ የማጣራት ስራ ለማከናወን የአውሮፕላን አደጋ መርማሪዎች ቡድን ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button