Breaking News

ሁለተኛው ኢትዮ ኪድስ የልጆች አዉደ ርዕይ በመኮንኖች ክበብ ተካሄደ፡፡

ሁለተኛው ኢትዮ ኪድስ የልጆች አዉደ ርዕይ በመኮንኖች ክበብ ተካሄደ፡፡

ሁለተኛው ኢትዮ ኪድስ የልጆች አዉደ ርዕይ በመኮንኖች ክበብ ተካሄደ፡፡

ለህጻናትና ታዳጊዎች የሚሆኑ ምርትና አገልግሎቶች ብቻ የቀረቡበትን አዉደ ርዕይ   በርካታ ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር በመሆን ጎብኝተውታል፡፡

ለህጻናትና ታዳጊዎች ታስቦ የተዘጋጀዉ አዉደ ርዕይ በመሆኑ የተለያዩ የህጻናት አልባሳት፣ መጻህፍት፣ ሲዲዎችና ዲቪዲ እንዲሁም የመጫወቻ ቁሳቁሶች በስፋት የቀረቡበት ነበር፡፡

በተጨማሪም አውደ ርዕዩን ለሚጎበኙ ህጻናት የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችም የቀረቡ ሲሆን የተለያዩ የህጻናት መጫወቻዎች እንዲሁም የሰርከስ ትርኢት እና የህጻናት ሙዚቃዎች  ቀርበዋል፡፡

በአውደ ርዕዩ ከህጻናት ጋር የተያያዙ ምርትና አገልግሎቶች ያሏቸው አምራቾች ፣አከፋፋዮች እና በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን ፤በህጻናት ልዩ ቁጠባ ላይ የተሰማሩ ባንኮችና የመድህን ድርጅቶች አገልግሎታቸውን አስተዋውቀዋል፡፡

ከህጻናት ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚሰሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚሰጡዋቸውን አገልግሎች አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የማስተዋወቅ ስራ ሰርተዋል፡፡

ኢትዮ ኪድስ የልጆች አውደ ርዕይ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በመሆን እየተዝናኑ የተለያዩ ምርቶችን በአንድ ቦታ የሚሸምቱበትና ድርጅቶችም በህጻናት ዙሪያ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ለማስተዋወቅ ሰፊ እድል እንዲያገኙ  የታለመ መሆኑን አዘጋጆቹ ነግረውናል፡፡

 

 

leave a reply