EthiopiaPolitics

68ኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በተለያዩ  ጉዳዮች ላይ ዉሳኔ አሳለፈ

68ኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በተለያዩ  ጉዳዮች ላይ ዉሳኔ አሳለፈ

የሚኒስትሮች  ምክር ቤት  ባካሄደው 68ኛ  መደበኛ ስብስባ  በተለያየ ጉዳዩች ላይ የተወያየ ሲሆን ፤ ከዚህ በፊት   ወጥቶ በነበረው የፀረ ሽብርተኝነት  አዋጅ በይዘት እና በአፈፃፀም  ክፍተቶች የነበሩበት  በመሆኑ  ጠቅላይ አቃቤ ህግ  የሌሎች ሀገራትን አለም አቀፍ ነበራዊ ሁኔታ ያገነዘበ  አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚነስትሮች ምክር ቤት  ውሳኔ አቅርቧል፡፡

ምክርቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ  ላይ በዝርዝር  ከተወያየ በኃላ ማሻሻያዎችን  በመጨመር  ለህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የተጨማሪ እሴት ታክስ  አዋጅን ለማሻሻል ተዘጋጅቶ በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮን ከግምት ውስጥ በማስገባት የአዋጁን አፈፃፀም  በአዲስ አዋጅ መተካት አስፈላጊ በመሆኑ  ፤ችግሩን ለመፍታት የገቢዎች ሚኒስቴር  እና የገንዘብ ሚኒስቴር የተጨማሪ እሴት ታክስን  አዋጅን ለማሻሻል  ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅተው  ለሚኒስትሮች ምክርቤት ውሰኔ አቅርበዋል፡፡

ምክርቤቱም በቀረበው  ረቂቅ አዋጅ ላይ  ከተወያየ በኃላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን  በመጨመር  ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት እንዲተላለፍ መወሰኑ ተነግሯል፡፡

ምክርቤቱ በቀረቡ ሶስት ከፍተኛ ደረጃ የመአድን   ማምረት  ስምምነት ፍቃዶች ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ  ስምምነቶቹ  በስራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button