EthiopiaSocial

ኢትዮጵያና ቻይና ግብርናን ጨምሮ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ያላቸዉን ግንኙነት አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያና ቻይና ግብርናን ጨምሮ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ያላቸዉን ግንኙነት አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ገለጹ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ  ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ ከቻይና የግብርናና የገጠር ልማት ምክትል ሚኒስትር ዶ/ር ቹ ዶንጁ ጋር በጋራ ትብብርን በማጠንከር ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ኢትዮጵያያና ቻይና ግብርናን ጨምሮ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ምሳሌ የሚሆን ጠንካራ ትብብር እንዳላቸው ዶ/ር ማርቆስ በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ አሁንም በርካታ ተግዳሮቶች ያሉበት መሆኑን ጠቅሰው ቻይና ያላትን የካበተ ልምድ ለኢትዮጵያ እንደታካፍልም ጠይቀዋል።

በተለይም በገበያ ትስስር፣ በግብርና ቴክኖሎጂ፣ በግብርና ፈጠራና መሰል ዘርፎች ኢትዮጵያ ልምድ ለመቅሰም ትፈልጋለች ብለዋል።

የቻይና የግብርናና የገጠር ልማት ምክትል ሚኒስትር ዶ/ር ቹ ዶንጁ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት በኩል ባለው ግንኙነት ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ያቀረቧቸውን ድጋፎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ግፊት እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

ምክትል ሚኒስትሩ ለመንግስታቱ ድርጅት የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ዳይሬክተር ጄኔራልነት እየተወዳደሩ መሆናቸውን በመግለጽ ቢመረጡ የሚያከናውኗቸውን ዋና ዋና እቅዶችም ለሚኒስትር ዴኤታው አብራርተውላቸዋል።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button