Africa

ግብፅ በመላ ሀገሪቱ ጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአስራአምስተኛ ጊዜ አራዘመች::

አዲስ አበባ፣ጥር 16፣ 2013  ግብፅ በመላ ሀገሪቱ ጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአስራአምስተኛ ጊዜ አራዘመች:: በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ተግባዋ የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አቃጅ ዳግም የታደሰው በፓርላመው ውሳኔና በፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ይሁንታ ነው፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ግብፅ የመጀመሪያውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጣለቸው እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2017 ነበር፡፡

በወቅቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገው የሽበርተኝነትን አደጋ ለመከላከል በሚል ምክንያት ሲሆን አሁንም ድረስ ስጋቶች ባለቀረፋቸው ለአስራ አምስተኛ ጊዜ ተራዝሟል ነው የተባለው:: ግብፅን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ ካበቋት ሁኔታዎች መካከል ዋነኛው በሁለት ቤተክርስቲያኖች ላይ በደረሱ የሽብር ጥቃቶች 45 ሰዎች መገደላቸው እንደነበር ተነግሯል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የግብፅ ባለሥልጣናት ሰዎችን ከአካባቢያቸው ማስነሳት፣ የሰዓት እላፊ ገደቦችን መጣል፣ እና ጥብቅ የደህንነት እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያስችላቸዋል ፡፡ በተጨማሪም የክልል የፀጥታ ኤጄንሲ አዋጁን የሚጥሱ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና ለማሰር ያስችለዋል፡፡ ግብፅ በሲናይ በረሃ ሽብተኞችን መዋጋት ከጀመረች ዓመታት የተቆጠሩ ሲሆን አሁንም ድረስ የአካባቢውን ችግር ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አልተቻላትም፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button