Uncategorized

የሱዳን ፖሊስ አልበሽርን ከእስር ለማስመለጥ የሞከሩ ሰዎች  አጋጥመውኛል አለ፡፡

የሱዳን ፖሊስ አልበሽርን ከእስር ለማስመለጥ የሞከሩ ሰዎች  አጋጥመውኛል አለ፡፡

ፖሊስ ባለፈው ሚያዚያ ወር ከስልጣናቸው የተወገዱት የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ደጋፊዎች በሚገኙበት የኮባር እስር ቤት ላይ ጉዳት በማድረስ ፕሬዝዳንቱን ለማስመለጥ ሲሞክሩ ተከላክያለሁ ብሏል፡፡

ፖሊስ በሰጠው መረጃ ወደ መቶ የሚጠጉ የአልበሽር እና አስተዳደራቸው ደጋፊዎች ያደረጉትን ሙከራ በማክሸፍ የተወሰኑትን በቁጥጥር ስር አውያቸዋለሁ ብሏል፡፡

ሙከራውን ያደረጉት ግለሰቦች በእስር ቤቱ ላይ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ በፖሊሶች እይታ ስር በመውደቃቸው ሀሳባቸው ሳይሳካ ቀርቷል ነው የተባለው፡፡

ሱዳናዊያን በህዝባዊ አመፅ የአልበሽርን መንግስት ቢያስወግዱም ቀድሞ የሳቸው ታማኞች የነበሩ ጄኔራሎች ስልጣኑን በመያዛቸው አሁንም ከፍተኛ ተቃውሞ ላይ ናቸው፡፡

በዚህም የተነሳ ከወታደራዊ ምክር ቤቱ የፀጥታ ሀይሎች ጋር ገርጭት ውስጥ በመግባታቸው በርካታ ሰዎች ህይዎታቸው አልፏል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button