PoliticsUncategorized

ሩዋንዳ እና ዩጋንዳ በመካከለላቸው የተፈጠረውን ውጥረት ማርገብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ሩዋንዳ እና ዩጋንዳ በመካከለላቸው የተፈጠረውን ውጥረት ማርገብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እና የሩዋንዳው አቻቸው ፖል ካጋሜ አንጎላ ውስጥ ተገናኝተው ነው ስምምነቱን የተፈራረሙት፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ሁለቱ ተጎራባች ሀገራት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዷ ሌላዋን ሰለልሽኝ በማለት በተደጋጋሚ ሲካሰሱ ነበር፡፡

በዚህም የተነሳ በጎረቤታሞቹ የድንበር አካባቢ የነበረው የንግድ እና የሰዎች ለሰዎች ግንኙነት እንቅስቃሴ እክል ገጥሞት ቆይቷል፡፡

ሩዋንዳ ጎረቤት ዩጋንዳን መሰረታቸውን ካምፓላ ያደረጉትን የሩዋንዳ ነፃነት እና ዲሞካራሲያዊ ሀይሎች የተባሉ ተቀናቃኞቸን በመደገፍ ተግባር ላይ ተሳትፋለች ብላ ከሳት ነበር፡፡

ከዩጋንዳ በኩልም በሩዋንዳ ላይ የተለያዩ ክሶች ሲሰነዘሩ የነበረ ሲሆን አሁን ሁለቱ መሪዎች ያደረጉት ስምምነት አንዱ የሌላውን ጠላት ላለመደገፍ፣ እንዲሁም የድንበር አካባቢ እንቅስቃሴዎች ወደነበሩበት እንዲመለሱ የሚለውን ያካትታል፡፡

ነፍጥ አንግበው የየሀገራቸውን መንግስታት በመውጋት ሰራዊታውን እየመሩ በሀይል ወደ ስልጣን የመጡት ካጋሜ እና ሙሴቬኒ ለዓመታት የልብ ወዳጆች የነበሩ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በመካከላቸው ነፋስ ገብቷል ነው የተባለው፡፡

ከፊርማው ስነስርዓት በኋላ ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ንግግር የተፈረመውን ስምምነት ለማክበር እና ተግባራዊ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button