Africa

ፖፕ ፍራንሲስ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀመሩ፡፡

ፖፕ ፍራንሲስ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀመሩ፡፡

ሶስት ሀገራትን የመጎብኘት መርሀ ግብር ተይዞላቸው ወደ  አፍሪካ የመጡት ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ የመጀመሪያ መዳረሻቸውን ሞዛምቢክ አድርገዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፖፑ ድህነት፣ የእርስ በርስ ግጭት እና የተፈጥሮ አደጋዎች የሚበዛባቸው ሶስት የአፍሪካ ሀገራትን ለመጎብኘት ነው ጉዟቸውን የጀመሩት፡፡

በዚህም መሰረት የሞዛምቢክ ቆይታቸውን እንዳጠናቀቁ ቀጣዩ ጉዟቸው ወደ ማዳጋስካር እና ሞሪሺየስ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

ፖፕ ፍራንሲስ ለጉዞ ከመነሳታቸው  አስቀድሞ ባስተለፉት መልእክት መላው አፍሪካዊያን በእርቅ እና በወንድማማችነት መንፈስ እንዲተባበሩ እና ሰላምን እንዲያሰፍኑ አደራ ብለዋል፡፡

በተለይ በሞዛምቢክ ያለው የሰላም እጦት እና በተደጋጋሚ በአውሎ ንፋስ አደጋ መመታት እንዳሳዘናቸውም ተናግረዋል፡፡

ሞዛምቢክ ሲገቡ በደማቅ ወታደራዊ ሰልፍ እና በባህላዊ የሙዚቃ እና የዳንስ ትርዒት የታጀበ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

በሶስቱም ሀገራት በሚያደርጓቸው ጉብኝቶች ከየ ሀገራቱ ባለ ስልጣናት ጋር ስለ ሰላም እና ስለ አንድነት በሰፊው ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button