Uncategorized

ዚምባቡዌ የነፃነት አባቷን በሞት ተነጠቀች፡፡

ዚምባቡዌ የነፃነት አባቷን በሞት ተነጠቀች፡፡

ዚምባቡዌን ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ የመሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሮበርት ጋብርኤል ሙጋቤ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር በ2017 ሙጋቤን በመፈንቅለ መንግስት አውርደው ከዚያም በምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የነፃነት አባታችንን አጣን በማለት ሀዘናቸውን ገልፀዋል፡፡

ሙጋቤ ካለፈው ሚያዚያ ጀምሮ ሲንጋፖር ውስጥ በህክምና ሲረዱ መቆየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳ በምእራባዊያን ዘንድ እንደ መብት ረጋጭ እና ጨቋኝ ተደርገው ቢታዩም ነጮች በቅኝ ግዛት ጊዜ በሀይል ያዙትን የጥቁሮችን መሬት ነጥቀው ለህዝባቸው በማከፋፈላቸው በብዙዎች ዘንድ አድናቆት ያገኙ መሪ ነበሩ፡፡

በፕሬዝዳንት ኤርሰን ምናንጋግዋ ቂም የያዙት ሙጋቤ ከሳምንት በፊት በተኙበት ሆስፒታል ሆነው  ስሞት ከእናቴ መቃብር ጎን ቅበሩኝ ምናጋግዋ በቀብሬ እንዳይገኝ የሚል ኑዛዜ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button