Africa

በናይጄሪያ በደረሰ ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ደርሷል ተባለ ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 በናይጄሪያ በደረሰ ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ደርሷል ተባለ :: በአህመድ ላዋን የተመራው የናይጄሪያ ሴኔት ልዑክ፤ በሳምንቱ መጨረሻ በገበሬዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች በተገደሉበት፤ የሰሜን ምስራቅ ቦርኖ ጉብኝት አድርጓል ፡፡ በተፈፀመው ጥቃት 43 አርሶ አደሮች መገደላቸው የተዘገበ ሲሆን ከአከባቢው ባለሥልጣናት ተሻሽለው እየወጡ ያሉ አኃዛዊ መረጃዎች የሟቾች ቁጥር ወደ 100 አድርሰዋል ፡፡

የቦርኖ ግዛት አስተዳዳሪ ባባጋና ዙሉም እሁድ ዕለት በተጎጂዎች የቀብር ሥነ ስርዓት ላይ ተገኝተዋል ፡፡ ከትናንት በስቲያ 43 ያህል ሰዎች የቀብር ስነስርዓታቸው የተፈፀመ ሲሆን ትናንት ጠዋት ግን የአካባቢውን ነዋሪ ሲጠይቅ ተጨማሪ 33 የቀብር ሥነ-ሥርዓቶች መፈፀማቸውን መረጃ አግኝተናል ሲሉ የቦርኖ ግዛት የኢንፎርሜሽን ኮሚሽነር ባባኩራ አባ ጆቶ ሰኞ ተናግረዋል ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ በቦርኖ ግዛት ውስጥ በዛባርማሪ ማህበረሰብ ውስጥ 110 ያህል አርሶ አደሮች በተጠርጣሪው የቦኮሃራም ታጣቂዎች ተገድለዋል ብሏል፡፡ ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ በምላሹ የሃገሪቱን የመከላከያ ኃይል የፀረ-ሽብር ውጊያ በታጣቂዎች ላይ እንዲወስድ ትዕዛዝ ስለማስተላለፋቸው ተነግሯል ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button