AfricaNews

የሁሉም የተፋሰሱ አባል አገራት በአባይ የመጠቀምና የመልማት ተፈጥሯዊ መብትም እውቅና ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ገለጹ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 የሁሉም የተፋሰሱ አባል አገራት በአባይ የመጠቀምና የመልማት ተፈጥሯዊ መብትም እውቅና ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ገለጹ
የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት  ሣህለ ወርቅ ዘውዴ  ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት  ፖል ካጋሜ ጋር በኪጋሊ ተገናኝተው በሁለትዮሽና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡

ፕሬዝደንት ፓል ካጋሜ በዚህ ወቅት ባደረገት ንግግር በአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል የሚደረገው የትብብር እንቅስቃሴ ከሁሉ በፊት ቴክኒካዊ ለሆኑ ጉዳዮች ቅድሚያ የሚሰጥና የሚደረጉ ትብብሮችም በዚህ ላይ የተመሰረቱ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡

በቴክኒካል ባለሙያዎች የሚቀርቡ ሳይንሳዊ ትንተናዎች እስከተያዙ ድረስ ውጤቱም የጋራ ፍላጎትን የሚያንጸባርቅ ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

የአባይ ጉዳይ የሁሉም ተፋሰስ ሀገራት ጉዳይ መሆኑን አጽንዎት ሰጥተው የተናገሩት ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ፤በወንዙ አጠቃቀም ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶችም በአፍሪካውያን የውይይትና የድርድር መድረኮች ሊፈቱ እንደሚገባ አመልክተዋል ፡፡

ለዚህም ስኬታማነት ሀገራቸው የሚጠበቅባትን አስተዋጽዎ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ፕሬዝዳንት ካጋሜ ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም መርህ እንዲሰፍን ጠንካራ አቋም ይዛ ከተቀሩት የተፋሰሱ ሀገራት ጋር በቅርበት ስትሰራ መቆየቷን ተናግረዋል ፡፡

በተለይም የአባይ ተፋሰስ ሀገራት እ.አ.አ ከ1999 ጀምሮ ለ10 ዓመታት ገደማ ሲያደርጉት የቆዩት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ዳር እንዲደርስ የተጫወተችው ሚና ከዚህ የጸና ቁርጠኝነቷ የሚመነጭ መሆኑንም  ፕሬዝዳንቷ አብራርተዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button