Ethiopia

በጎዳና ላይ የሚኖሩ 9 ሺህ ህጻናትን ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመቀላቀል የሚያስችል የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 በጎዳና ላይ የሚኖሩ 9 ሺህ ህጻናትን ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመቀላቀል የሚያስችል የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ። ፕሮጀክቱ በኤስ. ኦ .ኤስ የህጻናት መንደር ኢትዮጵያ የሚመራ ሲሆን ከመንግስት አካላት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ፣ አዳማና ድሬዳዋ ከተሞች የሚተገበር ይሆናል። በኢትዮጵያ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ካደረጉ ከ150 ሺህ በላይ ህጻናት መካከል 60 ሺህ የሚሆኑት በአዲስ አበባ እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።


የኤስ. ኦ .ኤስ ህጻናት መንደር የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ሰናይት ገብረእግዚአብሄር ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በኬንያ፣ ዩጋንዳና ሩዋንዳ እንደሚተገበር አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ብዛት ያላቸው ህጻናት በጎዳና ላይ መኖራቸውን ተከትሎ ከሌሎች ሀገራት በላቀ ፕሮጀክቱ የተለየ ትኩረት እንደተሰጠውም ገልጸዋል።

ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚውል 15 ሚሊዮን ዩሮ ከኖርዌይ የኤስ. ኦ .ኤስ  ህጻናት መንደር መገኘቱ ነው የተነገረው፡፡ በኢትዮጵያ  የኤስ. ኦ .ኤስ የህጻናት መንደር ዳይሬክተር ሳህለማሪያም አበበ ፕሮጀክቱ በጎዳና ላይ የሚኖሩ ህጻናትና ወጣቶችን ህይወት ለመቀየር ያለመ መሆኑን አስረድተዋል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ መንግስት በ10 አመቱ መሪ የልማት እቅድ ውስጥ ለማከናወን የያዛቸውን ተግባራት የሚደግፍ መሆኑን ነው የገለጹት።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button