crimeNews

የአማራ ክልል መንግሥት 7 ሺህ 650 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 የአማራ ክልል መንግሥት 7 ሺህ 650 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ፡፡

ክልሉ  የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በክልሉ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ያሉ 7 ሺህ 650 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱና የታራሚዎች ቁጥር እንዲቃለል የማድረግ ርምጃ መዉሰዱን አስታዉቋል፡፡የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዓለምሸት ምሕረቴ እንዳስታወቁት በየደረጃው ከሚገኙ ማረሚያ ቤቶች በጥንቃቄ ተለይተው እና በይቅርታ ቦርድ ተመርምረው የቀረቡ ታራሚዎች የይቅርታው ተጠቃሚ ተደርገው ነው የታራሚዎችን ቁጥር በመቀነስ የኮሮና ወረርሽኝን የመከላል ርምጃው የተወሰደው፡፡

በይቅርታ እንደፊቱ የሚደረጉ ታራሚዎችን ዝርዝር በተመለከተም ከሰው መግደል ውጭ በሆኑ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በመታረም ላይ የሚገኙ 12 የሚያጠቡ እናቶችና ሁለት ሕጻናትን ይዞ በመታረም ላይ የሚገኝ አንድ ወንድ ታራሚ፣ በአመክሮ የመፈቻ ጊዜያቸው እስከ አንድ ዓመት የቀራቸው 950 ታራሚዎች እና ቀላል ወንጀል ፈጽመው እስከ አንድ ዓመት የእስር ጊዜ የቀራቸው 6 ሺህ 684 ታራሚዎች፣ ከሰው መግደል ውጭ በሆኑ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በመታረም ላይ የሚገኙ ሦስት የውጭ ዜጋ ታራሚዎች እንደሚገኙበት አቶ ዓለምሸት አስታውቀዋል፡፡

የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንደዘገበዉ በይቅርታ ከሚፈቱት ታራሚዎች መካከል 7ሺህ 527 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 123 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን አቶ ዓለምሸት አመላክተዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button