COVID-19EthiopiaFeaturedHealthNews

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 92 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2012 በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 92 ደረሰበኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት በተደረገ 401 የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 7 ሰዎች መገኘታቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በዚህም እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 92 ከፍ ብሏል።ዛሬ በምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከአንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ በስተቀር ስድስቱ የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው። በዚህም መሰረት የ21 ዓመት እና የ51 ዓመት እድሜ ያላቻው ኢትዮጵያውን ከአሜሪካ የመጡ፤ እንዲሁም የ76 ዓመት እና የ34 ዓመት እድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከስዊድን የመጡ ሲሆን፥ ሁሉም በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

በተጨማሪም የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊ የጀርመንና የቤልጂየም የጉዞ ታሪክ ያለው እንዲሁም የ39 ዓመት ኢትዮጵያዊ ደግሞ ከጃፓን የመጣ ሲሆን፥ ሁለቱም በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ ናቸው።የ14 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ደግሞ የጉዞ ታሪክ እንደሌላት የተገለፀ ሲሆን፥ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንደነበራት በመጣራት ላይ የሚገኝ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
አሁን ላይ 72 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሲሆኑ፥ አንድ ሰው ደግሞ በጽኑ ህክምና ላይ የሚገኝ መሆኑን ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።ሚኒስትሯ መጭውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የሚካሄዱ የበዓል ግብይቶችም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ በጥንቃቄ እንዲከወኑም አሳስበዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button