AfricaCOVID-19crimeFeaturedHealthኢትዮጵያ

ሞሮኮ በማረሚያ ቤቶቿ ባደረገችው ምርመራ ከ300 በላይ ታራሚዎች በኮቪድ 19 መያዛቸውን አረጋገጠች::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 ሞሮኮ በማረሚያ ቤቶቿ ባደረገችው ምርመራ ከ300 በላይ ታራሚዎች በኮቪድ 19 መያዛቸውን አረጋገጠች::

ይሄ ቁጥር የተገኘው በሶስት እስር ቤቶች በሚገኙ 1 ሺህ 736 እስረኞች ላይ በተደረገ ምርመራ መሆኑን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል፡፡ከነዚህ ሶስት እስር ቤቶች መካከል ደግሞ 303 በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች የተገኙት በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በሚገኝ ኦዋራዛቴ በሚባል አንድ እስር ቤት ብቻ ነው፡፡

ምርመራው በተካሄደባቸው በሌሎቹ ሁለት እስር ቤቶች አስር ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ተገኝተዋል ነው የተባለው፡፡በሞሮኮ በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ ወደ 80 ሺህ የሚጠጉ ታራሚዎች የሚገኙ ሲሆን በፈረንጆቹ መጋቢት 16 እና ሚያዚያ 16 /2020 ባለው ጊዜ ብቻ ከ5 ሺህ 400 በላይ ሰዎች ወደ እስር ቤት መግባታቸው ታውቋል፡፡እስካሁን በሞሮኮ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ከነዚህ መካከል ደግሞ 165ቱ ህይዎታቸው አልፏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button