Ethiopia

የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት በተደረገው ጥረት መንግስት 124 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት በተደረገው ጥረት መንግስት 124 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ። የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያዘጋጀው የነዳጅ ግብይት ሪፎርም ትግበራ ማስተዋወቂያ መድረክ በሐዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ ያሉ ፈተናዎችን የሚዳስስ ሰነድ አቅርቦ ችግሮችን መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ ሪፎርሙ በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን በዘላቂነት ለመፍታት ወሳኝነት አለው።


በተለይ የትግበራ ሂደቱ እንዲሳካና ፍሬያማ እንዲሆን የፖለቲካ አመራሩን ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ ገልጸው፥ ዘርፉ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የግብይት ሥርዓቱን ማዘመን ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነም አንስተዋል፡፡ በሚኒስቴሩ የተነደፈው ሪፎርም የግብይት ሥርዓቱን ወደ ዓለም አቀፍ የግብይት ሥርዓት ለመቀየር ታስቦ መዘጋጀቱም ታውቋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button