EthiopiaSocial

ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ካላት ከፍተኛ አቅም አንጻር እምብዛም አልተጠቀመችም ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ካላት ከፍተኛ አቅም አንጻር እምብዛም አልተጠቀመችም ተባለ፡፡

ይህ የተባለው በኢትዮጵያ ያለውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማጎልበት የሚያስችል ስምምነት በኢትዮጵያ እና በአለም ባንክ መካከል በተፈረመበት ወቅት ነው፡፡

ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል  የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ሌንሳ መኮነን እና የኢንተርናሽናል ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጁሞኬ ጃጉን ተፈራርመዋል፡፡

ለሶስት አመታት የሚቆየው መርሃ ግብር ሀገሪቱ በኮንፍረንስ ቱሪዝም ዘርፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን ከማስቻሉም ባለፈ በዘርፉ የተሰማሩ የግል ድርጅቶችን አቅም ለማጎልበት ይረዳል ነው ያሉት ወይዘሪት ሌንሳ፡፡

የተለያዩ አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ስብሰባዎችና ኮንፍራንሶች ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ እንግዶች ያላቸው ቆይታ አጭር ነው ያሉት ዳይሬክተር ጁሞኬ፤ ቱሪስቶች በሀገሪቱ ያሉትን ታሪካዊ ፣ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ የቱሪዝም ሀብቶችን እንዲጎበኙ በማድረግ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ ይቻላል ብለዋል፡፡

በየአመቱ በቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ 10 ሚሊዮን መንገደኞች ይመላለሳሉ ከነዚህ መካከል 10 በመቶ ብቻ ናቸው ለተወሰነ ጊዜ ቆይተው ሀገሪቱን የሚጎበኙት መባሉንም ሰምተናል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button