AfricaCOVID-19News

በእስር የሚገኙ 3 የሱዳን የቀድሞ ባለስልጣናት በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ታወቀ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 በእስር የሚገኙ 3 የሱዳን የቀድሞ ባለስልጣናት በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ታወቀ::

በቫይረሱ ከተያዙት ግለሰቦች መካከል ሁለቱ በዳርፉር በተፈፀመው የጦር ወንጀል እጃቸው አለበት ተብለው በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚፈለጉ ናቸው ተብሏል፡፡ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በቫይረሱ የተያዙት የኦማር አልበሽር ረዳት የነበሩት አህመድ ሀሮን፣ የመከላከያና የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር የነበሩት አብደልራሂም ሞሀመድ ሁሴን እንዲሁም ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉት አሊ ኦስማን ናቸው፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ወንድም አሊ አልበሽርን ጨምሮ ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ናሙና ተወስዶ የምርመራ ውጤታቸው እየተጠበቀ መሆኑን የሀገሪቱ አቃቤ ህግ መስሪያ ቤት ተናግሯል፡፡ሱዳን እስካሁን ከ4 ሺህ 300 በላይ ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ ሲያዙባት ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡ሀገሪቱ ከአሁን ቀደም የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመቀነስ በማሰብ ከ4 ሺህ በላይ ፍርደኞችን ከእስር ፈትታለች፡፡የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ባለስልጣናት እና የቅርብ ሰዎች ጭምር በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው አሁንም እስር ቤት የሚገኙት መሆኑ ይታወቃል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button