Ethiopia

የነዳጅ እጥረት የተከሰተው ነዳጅን የማሸሽ ህገ ወጥ ተግባር እየተሰራ ስለሆነ ነው ተባለ

የነዳጅ እጥረት የተከሰተው ነዳጅን የማሸሽ ህገ ወጥ ተግባር እየተሰራ ስለሆነ ነው ተባለ

አርትስ 16/02/2011

በኢትዮጵያ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የተከሰተው የነዳጅ አቅርቦት ችግር ሰው ሰራሽ የሆነ ነዳጅን የማሸሽ ህገ ወጥ ተግባር በመከናወኑ እንደሆነ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተናገረ።

የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር  የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ እንደገለጹት፤ በምርት አቅርቦት ዙሪያ በሚፈጸም ደባ ያለምንም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት እጥረት እየተፈጠረ መሆኑን እና ነዳጅ የሚያከፋፍሉ ኩባንያዎች ከተፈቀደላቸው የነዳጅ ማራገፊያ ስፍራ ውጪ በማራገፍ እጥረቱ እንዲፈጠር ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

ይህ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ባለፉት ሳምንታት የነዳጅ እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑን ገልፀው፤  ነዳጅ በጥቁር ገበያ በበርሜልና በጄሪካን ጭምር እንዲሸጥ በማድረግ በኮንትሮባንድ የመነገድ ተግባርና ነዳጅ መልሶ ከአገር እንዲወጣ የማድረግ ህገ ወጥ ተግባር መስተዋሉን እና ነዳጅ የሚያጓጉዙ ኩባንያዎች ነዳጅ ከማደያ ውጪ መሸጥ እንደሌለባቸው አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ በማድረግ ወደ አገር ከምታስገባቸው ምርቶች ውስጥ አንዱ ነዳጅ ሲሆን በአመት 3 ቢሊዮን የአሜረካ ዶላር ታወጣለች።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button