News

ቦልሶናሮ የዓለም ጤና ድርጅትን ጥለው ሊወጡ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 ቦልሶናሮ የዓለም ጤና ድርጅትን ጥለው ሊወጡ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ ::የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ዣየር ቦልሶናሮ አሜሪካን ተከትለን ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነታች ለመውጣት ሁኔታውን ያእጠናነው ነው ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት የሀገራት መሪዎች ተጥለው የነበሩ የእንቅስቃሴ እገዳዎችን ለማንሳት መጣደፍ እንደሌለባቸው ማስጠንቀቁን ተከትሎ ነው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ ድርጅቱ በፖለቲካዊ አድልዎ ምክንያት ሁሉንም ሀገራት በእኩል ዓይን ማየት ካልቻለ አባልነታችንን እንሰርዛለን ሲሉ የማጠንቀቂያ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ቦልሶናሮ ድርጅቱን የከሰሱበት መንገድ ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተመሳሳይነት አለው ነው የተባለው፡፡ቫይረሱ በሀገሪቱ እያደረሰ ያለውን ከባድ ጥፋት ቀለል አድርገው በማየታቸው አሁን ላይ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የሞቱ ብዚላዊያን ቁጥር ከ35 ሺህ ማለፉ አብዝቶ እያስተቻቸው ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ፕሬዚዳት ቦልሶናሮ የግዛት አስተዳዳሪዎችን የእንቅስቃሴ ክልከላዎችን ለምን አላነሳችሁም በማለት አጥብቀው ሲወቅሱ ነው የሚታዩት፡፡ ብራዚል አሁን ላይ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ የተጠቁባት ሲሆን ይሄም ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በበሽታው ከተያዙባት አሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደድትቀመጥ አድርጓታል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button