AfricaNewsTourism

ፖፕ ፍራንሲስ በሊቢያ የሚካሄደው ውጊያ እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 ፖፕ ፍራንሲስ በሊቢያ የሚካሄደው ውጊያ እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ፡፡ የሮማው ሊቀጳጳስ ፍራንሲስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ባስተላለፉት መልዕክት እባካችሁ ይህች ሀገር ከብጥብጥ ወጥታ ወደ ሰላም ትመጣ ዘንድ አግዟት ብለዋል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ሊቀጳጳስ ፍራንሲስ በቅዱስ ጴጥሮች አደባባይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በሀገሪቱ እየተደረገ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ከልባቸው ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡ በሊቢያ በጄኔራል ከሊፋ ሀፍታር ጦርና በጠቅላይ ሚስትር ፋይዝ አልሳራጅ መንግስት መካከል ለአምስት ዓመታት ያህል በዘለቀው ውጊያ በርካቶችን ህይዎታቸውን አጥተዋል፤ ቤት ንብረታቸውን ጥለውም ተሰደዋል፡፡ ግብፅ በተፋላሚ ሀይሎቹ መካከል እርቅ እንዲወርድ አዲስ የሰላም ሀሳብ አለኝ ብትልም የትፖሊን
መንግስት የምትደግፈው ቱርክና ከሀፍታር ጎን ናት የምትባለው ሩሲያ በሚንስትሮች ደረጃ ሊደረግ የነበረውን ስብሰባ አራዝመዋል ነው የተባለው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button